በአማራብሔራዊ ከልላዊ መንግስት በሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ የገ/ኢ/ል/ዋ/ጽ/ቤት... Request for proposal Tender
3 years ago - Construction & Construction Machinery - Gondar - 519 viewsTender Details
በአማራብሔራዊ ከልላዊ መንግስት በሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ የገ/ኢ/ል/ዋ/ጽ/ቤት በ2010 የበጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የግንባታ ማቴሪያል ሲሚንቶ ብረታ ብረት እና የውሃ ዕቃ በመደበኛ በጀት ህጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑ ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የዘመኑንግብር የከፈሉበት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው።
- ከ50,000.00/ከሃምሳ ሺህ ብር/ በላይ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾችበጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋው 1% ማስያዝ የሚችል እና አሸናፊ ከሆነ በኋላ ከጠቅላላ ዋጋው 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ በመ/ሂ 1 በመቁረጥ ኮፒውን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለበት።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ የሚችል።
- አሽናፊ የሚሆነው ድርጅት ውል የሚወስደው በየዳ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ዋ/ጽ/ቤት እና ፍትህ ጽ/ቤት ይሆናል።
- አሸናፊ የሚለየው በሎት ወይም በጠቅላላ ድምር መሆኑን የተረዳ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ በማይመለስ ብር 30.00 /ሰላሳ ብር/ ብቻ ከረዳት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ከ16/4/2010 እስከ 30/4/2010 ዓ.ም በበየዳ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ዋ/ጽ/ቤት ዘወትር በማንኛውም ሰዓት እስከ 11፡30 ሰዓት በመምጣት ማግኘት ትችላላችሁ።
- የጨረታ ሳጥኑ በ1/5/2010 ዓ.ም ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ህጋዊ ተጫራች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የጨረታ አሸናፊው ያሸነፈውን ንብረት በወረዳው በግብርና ፑል ንብረት ክፍል ማስረከብ የሚችል።
- ጨረታውን ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታ ሰነዱን በተሰጠው ዝርዝር መሰረት ስርዝ ድልዝ በሌለው መሙላት የሚችል
- ለበለጠ መረጃ በጨረታ መመሪያው ወይም በስልክ ቁጥር፡- 0936237871 ጠይቀው መረዳት ትችላላችሁ።
በአማራ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት በሰ/ጎንደር ዞን አሰተዳደር የበየዳ ወረዳ የገ/ኢ/ል/ዋ/ጽ/ቤት
የግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት