Login for faster access to the best tenders. Click here if you don't have an account.

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ እስተዳደር ዞን የላስታ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በ... Request for bid Tender

7 months ago Automotive Spare Parts, Tyre and Related Desē 75 views
Tender Details

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ እስተዳደር ዞን የላስታ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በላስታ ወረዳ ወሰጥ ከሚተዳደሩት ቀበሌዎች አንዱ በሆነው በአቡኒዮሴፍ ቀበሌ እስኒየሴፍ ተራራ ላይ ለህዋ ምርምር አገልግሎት የሚውል የቤቶች ግንባታ ስራ በህዋ ምርምር በጀት እና ለላ ወ/ሴ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የመኪና ጎማ በመደበኛ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግገር መፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው::

1. በአዲሱ የንግድ አዋጅ መሠረት የእያንዳንዱ ሎት የተናጠል በዘመኑ የታደሰ ንግድ

ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ነምበር ሰርተፍኬት ያሳቸውና፣ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡

2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ለመኪና ጎማ የማይመለስ የኢት.ብር 35.00 /ሰላሳ አምስት ብር ብቻ እና ለህዋ ምርምር ቤት ግንባታው 100/ አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፍል ላስታ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁ 3 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃ እና ግንባታ ለጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 20% በጥሬ ገንዘብ ወይም ከባንክ በተረጋገጠ CPO ለእያንዳንዱ የጨረታ ዓይነት ለየብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከፖስታው ውስጥ አብሮ መግባት ወይም ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡

4 የቤት ግንባታ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን አንስቶ የሚቆጠር 21 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በ22ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾት ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን እንዲሁም የመኪና ጎማ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን አንስቶ የሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

5. የተጠቀሰው ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም በካላንደር ዝግ ከሆነ ለሚቀጥለው የስራ

ቀን በተመሣሣይ ስዓት ይተላለፍና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ላስታ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 ይከፈታል፡፡

6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን ኮፒና ኦርጅናል በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ስዓት ውስጥ ማስገባት አለባቸው::

7. እሸናፊው አካል እቃዎችን በራሱ ትራንስፖርት ላስታ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

8. የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቶች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡

9. በዚህ ጨረታ ላይ የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች ቅድመ ክፍያ የማይጠይቁ እና ክፍያን በሚመለከት ግንባታውን እየገነባ በሚያልቁ ስራዎች ላይ የተሰሩት ስራዎች እየታየ/

በሚመለከተው አካል እየተረጋገጠ ክፍያው የሚከፈል መሆኑን መታወቅ አለበት፡፡

10. አሸናፊው አካል ማሸነፉ ከተገለጸለት በኋላ የግንባታ ስራውን ከጀመረበት ከሶስት ወር እስከ አራት ወር ባለው ውስጥ ግንባታውን አጠናቆ የሚያስረከብ መሆን አለበት፡፡

11. ግንባታውን በተገቢው ሁኔታ ሰፕላኑ መሰረት በሚጠይቀው ማቴሪያል ጥራቱን

በጠበቀ መልኩ ሰርቶ የሚያስረክብ መሆን አለበት

12. በዚህ የቤት ግንባታ ላይ መወዳደር የሚችሉት ኮንትራክተሮች ከደረጃ 8 ከስምንት/ እና በላይ መሆን አለባቸው፡፡

13 ተጫራቾት በአንድ ሎት ውስጥ የተዘረዘሩትን የእቃ አይነቶች ከፋፍሎ መሙላት አይቻልም ውድድሩ በየሎት ምድቡ ጥቅል ብር ወይም ድምር ስለሆነ የሁሉም ዋጋዎች መሞላት አለበት፡፡

14 መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ

የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው ::

15. የተሞላው ዋጋ ጸንቶ የሚቆይበት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን አንስቶ በሚቆጠር ገዝቅተኛ ቀን ከ40 ቀናት በላይ ጸንቶ ይቆያል፡፡

16. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ወይም ማብራሪያ ከፈለጉ በእካል በመቅረብ ወይም ከዚህ በታች በተጠቀሱት ስልክ ቁጥሮች 0333360277 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን የላስታ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት

Company Description
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን የላስታ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት

 
Location