በኢ/ኤ/አገልግሎት የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም ኦሮሚያ ሪጅን ቢሮ የገጠር ከተሞ... Request for bid Tender
10 months ago - Rental - Nazrēt - 143 viewsTender Details
በኢ/ኤ/አገልግሎት የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም ኦሮሚያ ሪጅን ቢሮ የገጠር ከተሞችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ የመካከለኛ የጭነት ተሽከርካሪዎችን በመከራየት ለዲስትሪቢውሽን መስመር ዝርጋታ ስራ የሚያገለግሉ እቃዎችን፣ ምሰሶዎችን እና የቀን ሠራተኞችን የማጓጓዝ ሥራዎችን ለማከናወን የሚችሉአይሱዙ ተሽከርካሪዎች ብዛት 4 (አራት) በጨረታ አወዳድሮ አሸናፊዎችን በኪራይ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር OR-UEAP/NCB/02/2012
ስለሆነም ማንኛውም በዘርፉ የተሰማሩ ትራንስፖርተሮች መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል፡፡
1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት፤ ዓመታዊ የቴክኒክ ምርመራ ያከናወኑበትን (ለ2012 እና 2013) ዓ.ም ማሰራት የሚችል ቦሎ እና የተሽከርካሪዎቹን የኢንሹራንስ ዋስትና ማስረጃ ሶስተኛ ወገን (ለ2012 እና 2013) ዓ.ም ማሰራት የሚችል ከሚመለከተው ባለስልጣን የመንግስት መ/ቤት ማቅረብ አለባቸው::
2 ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 150.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. አድራሻ፡- አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ፊት ለፊት በሚገኘው አማጋ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 06፡፡
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በተመለከተ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በዝርዝር ተቀምጧል፡፡
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላትና በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ጨረታ ቁጥር 0R-UEAP/NCB/02/2012 የሚል ምልከት በማድረግ እስከ መጋቢት 1 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 8.00 ሰዓት ድረስ አማጋ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የሪጅኑ ሲሮ በመምጣት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም መጋቢት 1 ቀን 2012 ዓም ቢሪጅኑ ሰፕላይ ቼይን ቢሮ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፣ ፣
7. የፕሮግራም ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
8. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-5575209/011-5573898 መደወል ይችላሉ፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም ኦሮሚያ ሪጅን ቢሮ