Login for faster access to the best tenders. Click here if you don't have an account.

በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ቂሊንጦ ለስራ አገልግሎት የሚ... Request for bid Tender

3 months ago Building Materials Addis Ababa 44 views
Tender Details

በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ቂሊንጦ ለስራ አገልግሎት የሚውል ልዩ ልዩ የጥገና እቃዎች፣ሲሚንቶ፣ሚስማር ባለ 12፣ሚስማር ባለ 10፤ሚስማር ባለ 9፣የቆርቆሮ ሚስማር፤ቡሩሽ 4X14፣ፍሎረሰንት እምፖል ባለ 18 ዋት፣ፍሎረሰንት ባለ 18 ዋት ኮምፕሌት፤ተንጠልጣይ ሶኬት፣ማብሪያና ማጥፊያ ተንጠልጣይ፣ፍሎረሰንት እምፖል ባለ 36 ዋት፣ እስታተር ኤስ ቱ፣ ኮኔክተር ባለ 45mm፣ ማስተር ቴስት ላይት ትልቁ፣የኤሌክትሪክ ገመድ ባለ 2.5፣ ከሮም ጌት ቫልቭ /2፣ኩሮም ጌት ቫልቭ 3/4፣ሩቬኔቶ 3/4፣ኤልቦ የብረት /2 ፣ሩቬኔቶ /2፤ጌት ቫልቭ 42፣ጌት ቫልቭ 3/4፣ሮዲሰር የብረት ወደ 1/2፣ፒፒ ኤልቦ ባለ 50፤ፒፒሲ ዘንግ ባለ 50፣ፒፒሲ ባለ 10 ዘንግ፤ፒፒሲ ኤልቦ 10፤ፒፒሲ ዘንግ 1/2 ፤ ተንጠልጣይ ቁልፍ ትልቁ 266፣ተንጠልጣይ ቁልፍ ትንሹ 265፤ሰረገላ ቁልፍ፤ ናስትሮ፣ብሬከር ስሪፌዝ ባለ 63 አምፔር፤ብሬከር ባለ 25 እምፔር፣ፓውዛ አምፖል ባለ 1500፣ፓውዛ ባለ 1000 ዋት፣፣ፓውዛ ባለ 500 ዋት፤ ሽክላ ምጣድ ባለ 58 የተቦረቦረ ማሀልና ዳር፣ኮንዲት ባለ 18፤ መሸጎሪያ፣ ልመጥ ላሜራ ባለ 1.5mm፣ ትበላሬ ባለ 20 2mm፣ትበላሬ ባለ 30 2mm፣ ኤል ባለ 38 2mm፣እንትረስት ቀለም ቀይ እና ግሬየ፣ብሬከር 400 አንፔር፣ሬዚስታንስ ባለ 0.9mm፤ኤሌክትሮድ ባለ2.5mm፣ ቶርኖ ማጥፊያ፣ የመበየጃ መነፅር፤ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ስውል መግዛት ይፈልጋል።

በጨረታው መሣተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መመሪያና መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው የተገለፀ መሆን አለበት::

2. የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ

3. የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው::

4. የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል አቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከገቢዎች ጉምሩክ ባለስልጣን የዘመኑን ግብር ከፍለው ስለማጠናቀቃቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው::

5. ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆኑ በጨረታው ለመሳተፍ ከአደራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፣

6. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00/ ሃምሳ ብር/ በኢትዩጵያ ንግድ ባንክ በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ስም በአካውንት ቁጥር 1000007971347 ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ሥራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችና የዋጋ ማቅረቢያዎችንፋይናንሻል ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለበት፡፡ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ በአንድ ላይ አሽጎ ያቀረበ ተወዳዳሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ውጭ ይደረጋል፡፡

8. ማንኛውም ተጫራቾች የሚያስገቡት ሰነድ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናሉን እና ኮፒውን ለየብቻ እንዲሁም ፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናሉን እና ኮፒውን ለየብቻ በተለያዩ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የሚጫረቱበትን የጨረታ ሰነድ ቁጥር በትክክል መፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ እና በሁለም የመጫረቻ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተም በመምታት ማስገባት ያለባቸው ሲሆን ስርዝ ድልዝ፣ በፍለድ የጠፋ ሰነድ፣ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የለውም::

9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያስይዙት ሲፒኦ ከቴክኒክ ሰነዶች ከኦርጅናሉ ጋር በአንድ ላይ አሽገው ማቅረብ አለባቸው::

10. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 / ሃያ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ሥም አዘጋጅተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ እስከ ጥቅምት 02 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 500 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው እንዲሁም የባንክ ዋስተና የሚያስይዙ ተጫራቾች የቆይታ ጊዜው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 90 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርበታል፡፡

11. ጨረታው ጥቅምት 02 ቀን 2013 ዓም ከቀኑ 5፡30 ሰዓት ተጫራቶች ወኪሎቻቸው/በተገኘበት ቂሊንጦ በሚገኘው በመ/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል።

12. የጨረታው ዝርዝር መመሪያ በጨረታ ሰነዱ ተዘርዝሮ ቀርቧል፡፡

13. አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ እይቻልም እንዲሁም ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።

14. መስሪያ ቤቱ የታሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ቀጠሮ ማረፊያ ቤት እስተዳደር እለ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ አጠገብ

ለበለጠ መረጃ ፡- 0114 71 63 33 /0118 88 60 89/011 434 89 86 ደውለው ጠየቅ ይቻላል

በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር

የቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር/ ቂሊንጦ

Company Description
በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር

 
Location