ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. ስመ ጥር እና ታዋቂ በሆኑ ኢትዮጵያውያን ባለሃብቶች እና ድርጅቶች በ... Request for proposal Tender
3 weeks ago - Public Relations & Advertising - Addis Ababa - 23 viewsTender Details
ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. ስመ ጥር እና ታዋቂ በሆኑ ኢትዮጵያውያን ባለሃብቶች እና ድርጅቶች በጥቅምት ወር 2003 ዓ.ም. ተመስርቶ ለህብረተሰቡ ህይወት ነክ ያልሆነ የኢንሹራንስ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ እና ከጊዚ ወደ ጊዜ የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት በዘርፉ በቂ እውቀትና ክህሎት ያላቸውን ባለሙያዎች በመቅጠር ለህብረተሰቡ ቀልጣፋና አስተማማኝ የሆነ የኢንሹራንስ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ኩባንያውን ለህብረተሰቡ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ይረዳ ዘንድ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ማስታወቂያዎችን በዕውቅ ባለሙያዎች ለማሰራት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች በዝርዝር በቀረቡት መስፈርቶች መሰረት በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች እና ባለሙያዎች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች፡
1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በዘርፉ የተሰማሩበትን የታደሰየንግድ ፈቃድ፣ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው እና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች ስለጨረታው የሚገልፀውን ሠነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ጠመንጃ ያዥ ግሎባል ሆቴል ፊትለፊት በሚገኘው የብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ ዋናው መ/ቤት የሺታም ህንፃ አራተኛ ፎቅ የሰው ሃብት እና ንብረት አስተዳደር በመገኘት እስከ ጥር 5 ቀን 2013 ዓ.ም የማይመለስ ብር 100 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ሲመልሱ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 2% የባንክ ጋራንቲ ወይም በባንክ በተረጋገጠ CPO በብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ ስም አዘጋጅተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ተተይቦ ወይም በጉልህ የእጅ ጽሁፍ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
5. የጨረታ ሰነዱ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን (የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዱን ያካተተ) እስከ ጥር 5 ቀን 2013 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
7. ጨረታው ጥር 5 ቀን 2013 ዓ.ም በ8፡30 ሰዓት 4ተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኩባንያው መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
8. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ
ዋናው መ/ቤት
የሺታም ህንፃ 4ተኛ ፎቅ
ደብረዘይት መንገድ፣ በቅሎ ቤት ግሎባል ሆቴል አካባቢ
ከገቢዎች ሚኒስቴር ፊት ለፊት
ስልክ: 0114-674431 / 0930011347
ፋክስ: 0114-668701
ዌብሳይት:www.berhaninsurance.com
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ