ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ (ኖክ) በሀገራችን የፔትሮልየም ውጤቶች ገበያ ዘርፍ የመሪነቱን ስፍራ የ... Request for bid Tender
2 years ago - Minerals and Natural Resources - Gondar - 361 viewsTender Details
ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ (ኖክ) በሀገራችን የፔትሮልየም ውጤቶች ገበያ ዘርፍ የመሪነቱን ስፍራ የጨበጠና በዓይነታቸው ዘመናዊ እና ለአገልግሎት አሰጣጥ ምቹ የሆኑ የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎችን ስትራቴጂያዊ በሆኑ የተለያዩ የአገሪቱ ስፍራዎች ላይ በመገንባት ህብረተሰቡ የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኝ በማድረግ ፈር ቀዳኛ ሚና የተጫወተ ሐገር በቀል ኩበንያ ነው::
ኩበንያችን በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያላቸውን የካልቴክስ ብራንድ የሆኑትን የተሽከርካሪና የኢንደስትሪ ዘይትና ቅባቶችን ለጎንደር ከተማና አከባቢዋ ለሚገኙ ደንበኞቻችን የሚያከፋፍል ወኪል ይፈልጋል::
ይህንን እድል በሃላፊነት በመውሰድ እና በተሻለ መልክ ለተጠቃሚ ተደራሽ እናደርጋለን የሚሉ አመልካቾቸ ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀውን ቅፅ በዋናው መስሪያ ቤት 2ኛ ፎቅ በግንባር ቀርቦ በመውስድ ስራውን ለማከናወን የምትችሉ መሆኑን ከሚያሳዩ ማስረጃዎች ጋር በማያያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በ 10 (አስር) የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ ሰነዶቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን::
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡
ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ ኃ.የተ.የግ (ኖክ)
የሪቴይል ማርኬቲንግ ክፍል - 011-662-2907 ይደውሉ::
Company Description
ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ