አንበሳ ጫማ አክስዮን ማህበር ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተዘረዘሩትን የሰራተኛ የደንብ ልብስ በጨ... Request for bid Tender
1 month ago - Textiles & Leather Products - Addis Ababa - 24 viewsTender Details
አንበሳ ጫማ አክስዮን ማህበር ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተዘረዘሩትን የሰራተኛ የደንብ ልብስ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ | የልብሱ ዓይነት | መለኪያ | ብዛት |
---|---|---|---|
1 | ካኪ ጋወን ( ኦሊቭ ግሪን ጋዎን) | በቁጥር | 30 |
2 | ሰማያዊ ጋወን (ብሉብላክ ጋዎን) | በቁጥር | 2 |
3 | ሰማያዊ ጋወን (ብሉብላክ ጋዎን) | በቁጥር | 8 |
4 | ሰማያዊ ኮትና ሱሪ | በልኬት | 108 |
5 | ነጭ ቴትሮን ጋወን | በቁጥር | 56 |
6 | ካኪ ሰማያዊ ጋወን (ብሉብላክ ጋዎን) | በቁጥር | 54 |
7 | ሰማያዊ ኮት ( ብሉብላክ ጋዎን ካኪ) | በቁጥር | 32 |
8 | ሰማያዊ ጋወን (ብሉብላክ ጋዎን) | በቁጥር | 448 |
9 | ሀምራዊ ቲሸርት እጅጌ ሙሉ | በቁጥር | 572 |
10 | አርንጓዴ ቲሸርት እጅጌ ሙሉ | በቁጥር | 756 |
11 | ቢጫ ቲሸርት እጅጌ ሙሉ | በቁጥር | 60 |
12 | ሰማያዊ ኮትና ሱሪ (ብሉብላክ ቴትረን ጨርቅ) | በልኬት | 50 |
13 | ሰማያዊ ኮትና ሱሪ (ቴትረን ጨርቅ ብሉብላክ) | በቁጥር | 122 |
14 | ሰማያዊ ኮፍያ ብሉብላክ | በቁጥር | 122 |
15 | አርንጓዴ ኮትና ሱሪ (ቴትረን) | በቁጥር | 50 |
16 | ብትን ጨርቅ(ቴትረን6000) | በሜትር | 798 |
17 | ሸሚዝ(ሰማያዊ ስትራይፕ ሸሚዝ) | በቁጥር | 532 |
18 | ኮትና ሸሚዝ(ቴትረን ጨርቅ ብሉብላክ) | በልኬት | 122 |
ስለሆነም ተጫራቾች፡-
1. በመስኩ የ2013ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
2. የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (TIN)እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና የዘመኑን የግብር ግዴታ የተወጡ ፣ የከፈሉበትን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ ፣ በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን መረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
3. የጨረታ ማስረከቢያ ገንዘብ ብር 10,000 (አስር ሺ) በካሽ ወይም በሲ.ፒ.ኦ ከደረሰኝ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4. የጨረታ ሠነዱን ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል አቃቂ ከሚገኘው ዋና መ/ቤት ፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ መግዛት ይቻላል፡፡
5. ከላይ የተገለፁትን ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአግባቡ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 8፡00 ድረስ ብቻ አክስዮን ማህበሩ በሚገኝበት በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቀበሌ 02 የቤት ቁጥር 202 በሚገኘው ዋና መ/ቤት በአቅርበት መምሪያ ቢሮ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ይከፈታል፡፡
7. ሁሉም የደንብ ልብሶች ላይ የድርጅቱን አርማ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡