የጎን/ከ/አስ/መንገዶች ባለሥልጣን ለ2010 በጀት አመት የማሽነሪዎችና የተሸከርካሪዎች ጎማ በግ... Request for bid Tender
11 months ago - Automotive Spare Parts, Tyre and Related - Gondar - 128 viewsTender Details
የጎን/ከ/አስ/መንገዶች ባለሥልጣን ለ2010 በጀት አመት የማሽነሪዎችና የተሸከርካሪዎች ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሚሉተጫራቶችመወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያለው የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት/ ከፋይ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ ፊርማና ማህተም አድርገው አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርቡት ከጠቅላላ ዋጋ ላይ 1% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለበት
6. ማንኛውም ተጫራች ለመግዛት የፈለገውን የጨረታ ሰነድ በጎ/ከ/አስ/ከንቲባ ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ጎ/ከ/አስ/ መንገዶች ባለሥልጣን ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በመምጣት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) መግዛት የሚችል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
7. ጨረታው ኣየር ላይ የሚውልበት ቀን ከየካቲት 19 ቀን 2012 ዓ.ም እስከ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ.ም ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን መጋቢት3ቀን 2012 ዓ.ም ከጧቱ 4፡00 ስዓት ታሽጎ በ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ ፡- መ/ቤቱ የተሻለ እማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 0581260204/0581260205
በአብክመ የጎንደር ከተማ አስተዳደር
መንገድ ባለስልጣን